ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች
የትኞቹ የንግድ ዓይነቶች ለWashington Small Business Flex Fund 2 (ዋሽንግተን አነስተኛ ቢዝነስ ፍሌክስ ፈንድ 2) ብድር ብቁ ናቸው?
ለFlex Fund ብድር ብቁ ለመሆን አንድ አነስተኛ ንግድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት። የቅድመ ማመልከቻው የንግድ ሥራው ትልቁ የባለቤትነት ድርሻ ባለው ባለቤት መሞላት እና መቅረብ እንዳለበት እና ከ20% በላይ የባለቤትነት ድርሻ ያላቸው ሁሉም ባለቤቶች የቀረበውን መረጃ ማረጋገጥ እንዳለባቸው እባክዎ ልብ ይበሉ።
አንድ የንግድ ድርጅት ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በዚህ ፕሮግራም መሠረት ብድር ለማግኘት ብቁ ሆኖ እንዲቆጠር የሚያስፈልገው ዝቅተኛ መስፈርት የሚከተለው ነው፦
- – የንግድ ድርጅቱ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት 50 ወይም ከዚያ ያነሱ ሰራተኞች መቅጠር አለበት፤
- – ማመልከቻው ከገባበት ቀን በፊት ቢያንስ ለአንድ አመት ሲሰራ የቆየ መሆን አለብት
- – ከ5 ሚሊዮን ዶላር ያነሰ ዓመታዊ ገቢ ሊኖረው ይገባል
- – ባለፈው እና በታቀደው የገንዘብ ፍሰት በመጠቀም ብድሩን የመክፈል አቅም ማሳየት አለበት
- – በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ ነባር ስራዎች ሊኖረው ይገባል
ይህ ፕሮግራም ከሌሎች የብድር ፈንዶች የሚለየው እንዴት ነው?
ለትርፍ ያልተቋቋሙ የማህበረሰብ-ተኮር አበዳሪዎች አውታረ መረባችን የWashington Small Business Flex Fund 2 ከሌሎች የብድር ፕሮግራሞች የተለየ ያደርገዋል።
የዋሽንግተን አነስተኛ ንግዶች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን በመርዳት የአስር ዓመታት ልምድ ያላቸው እነዚህ የማህበረሰብ አበዳሪዎች በብድር ሂደቱ በእያንዳንዱ ደረጃ ሊረዱዎት ይችላሉ።
መስያዣ ያስፈልገኛል?
ብቁ ለመሆን ምንም የተለየ መስያዣ አያስፈልግም። ለየትኛውም የተለየ ሪል እስቴት ወይም መሳሪያ መዳረሻ ሊኖርዎት አይገባም። ይሁን እንጂ በንግድ ንብረቶች ላይ ጠቅላላ የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ የዋስትና ማረጋገጫ ይቀርባል፣ እና አበዳሪዎ ተጨማሪ፣ የተወሰነ መስያዣ ሊጠይቅ ይችላል። 20% ወይም ከዚያ በላይ የንግድ ሥራ ባለቤት ለሆኑ ግለሰቦች የግል ዋስትናዎች ያስፈልጋሉ።
ለማመልከት የእኔ ንግድ መሰረቱ በዋሽንግተን ውስጥ መሆን አለበት?
አዎ፣ በዋናነት ከብድሩ ተጠቃሚ የሆነው ዋና ቢሮ ወይም የንግዱ መገኛ በዋሽንግተን ውስጥ መሆን አለበት፣ እና የታሰበው ገንዘብ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት በዋሽንግተን ነው።
የአካባቢው ማህበረሰብ-ተኮር አበዳሪዎች እነማን ናቸው?
ለትርፍ ያልተቋቋሙ የማህበረሰብ-ተኮር አበዳሪዎች አውታረ መረባችን የWashington Small Business Flex Fund 2 ከሌሎች የብድር ፕሮግራሞች የተለየ ያደርገዋል። የዋሽንግተን አነስተኛ ንግዶች እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን በመርዳት የአስር ዓመታት ልምድ ያላቸው እነዚህ የማህበረሰብ አበዳሪዎች በብድር ሂደቱ በእያንዳንዱ ደረጃ ሊረዱዎት ይችላሉ።
ለምንድነው ማመልከቻው ስለ የግል ያለፈ ታሪኬን የሚጠይቀው?
በWashington Small Business Flex Fund 2 በኩል የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ማህበረሰቦችን እና አነስተኛ ንግዶችን እና እንዲበለጽጉ የሚረዱ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን ለማጐልበት ያለመ ነው። አመልካቾች በፈቃደኝነት የሚያቀርቡት ያለፈ ታሪክ መረጃ ፕሮግራሙ የገንዘብ ድጋፍ በጣም ለሚያስፈልጋቸው አነስተኛ እና አካባቢያዊ ንግዶች መድረሱን ለማረጋገጥ ይረዳናል።
ከብድር ማመልከቻው ጋር በተያያዘ እርዳታ ቢያስፈልገኝስ?
SmallBusinessFlexFund.orgን ሲጎበኙ ማመልከቻውን በሚያቀርቡበት እያንዳንዱ ደረጃ ላይ ሊረዳዎ እና ወደ ተጨማሪ የድጋፍ አገልግሎቶች ሊያመራዎ ከሚችል አካባቢያዊ ማህበረሰብ-ተኮር አበዳሪ ጋር ይገናኛሉ።
የብድርሩ ውሎች ምንድን ናቸው?
ከ36 እስከ 72 ወራት የብድር ውሎች
እስከ 250,000 ዶላር ድረስ ይበደሩ
ከWSJ ዋና ተመን በ1-4% ከፍ ያሉ ተመኖች
ለብድሩ ዕድሜው ቋሚ የወለድ መጠኖች
የቅድመ ክፍያ ቅጣቶች የሉም
ብድሩን ምን ልጠቀምበት እችላለሁ?
የWashington Small Business Flex Fund 2 ብድሮች የሚከተሉትን ጨምሮ ለተለያዩ የንግድ ፍላጐቶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፦
- ደሞዝ
- – ኪራይ እና መገልገያዎች
- – የሕንጻ ማሻሻያዎች ወይም ጥገናዎች
- – ግብይት እና ማስታወቂያ
- – ቁሳቁሶች እና ሌሎች የንግድ ወጪዎች
ብድሮች ለሚከተሉት ጥቅም ላይ ሊውሉ አይችሉም፦
- – የተገብሮ የሪል እስቴት ኢንቨስትመንቶች
- – የሎቢ እንቅስቃሴዎች
- – በዋስትና ግብይቶች ውስጥ መሳተፍ
- – በፌዴራል ወይም በዋሽንግተን ግዛት ሕግ የተከለከሉ ተግባራት ወይም ሌሎች የተከለከሉ ተግባራት
ማመልከቻዎን በሚያቀርቡበት ጊዜ ለህብረተሰቡ አበዳሪ የቀረበውን የብድር አገልግሎት ለመጠቀም የቀረበውን ሃሳብ በዝርዝር መግለጽ ያስፈልግዎታል።
ለማመልከት ብቁ ከሆንኩ ለብድር ማፅደቄ ዋስትና አለኝ?
በማመልከቻዎች ብዛት ላይ በመመርኮዝ ሁሉም አመልካቾች ብድር ማግኘት ላይችሉ ይችላሉ። ማመልከቻዎች በየደረጃው ይገመገማሉ። በተጨማሪም፣ ሁሉም ብድሮች በራሳቸው የብድር ውሳኔዎች ኃላፊነት ባላቸው ተሳታፊ ማህበረሰብ አበዳሪዎች የዋስትና ለማረጋገጫ ግምገማ እና ማጽደቅ ተገዢ ናቸው።
ይህ ድረ-ገጽ ብድር ለመስጠት የቀረበ ቅናሽ ወይም ቁርጠኝነት አለመሆኑን እባክዎ ልብ ይበሉ። ሁሉም ተመኖች እና የብድር ውሎች ሊለወጡ ይችላሉ።
ለWashington Small Business Flex Fund 2 ብድር ለማመልከት ምን መረጃ ያስፈልጋል?
እንደ ሙሉ የብድር ማመልከቻዎ፣ ለማህበረሰብ አበዳሪው የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ያስፈልግዎታል፡-
- – ሁለት የቅርብ ጊዜ የቀረቡ የግብር ተመላሾች፣ ካለ እና በአበዳሪው ከተፈለገ;
- – የባንክ መግለጫዎች እና/ወይም ከውስጥ የመነጩ የፋይናንስ መግለጫዎች፤
- – ስም፣ አድራሻ፣ የማህበራዊ ዋስትና ቍጥር(SSN)፣ የአሠሪ መታወቂያ ቍጥር(EIN) ወይም የግለሰብ ግብር ከፋይ መታወቂያ ቍጥር(ITIN)፣ የስልክ ቍጥር፣ ኢሜይል፣ መቶኛ ባለቤትነት እና የፎቶ መታወቂያ ጨምሮ ከ 20% በላይ ባለቤትነት ያላቸው የንግድ ባለቤቶች መረጃ;
- – የተፈፀመ የማረጋገጫ ቅጽ (በማህበረሰብ አበዳሪው የሚቀርብ);
- – የንግድ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋመ አካል ህጋዊ ምስረታ ማስረጃ (ለምሳሌ, የመዋቅር አንቀጾች እና መተዳደሪያ ደንቦች);
- – የግል ዋስትና (ለንግድ ሥራ ብቻ); እና
- – ማመልከቻው በሚቀርብበት ጊዜ ወይም ከዚያ በኋላ በማህበረሰቡ አበዳሪ የሚጠየቁ ሌሎች ሰነዶች።
አስፈላጊውን ሰነድ ለመሰብሰብ፣ ማንኛውንም የብድር ፍተሻ ለማካሄድ እና የማመልከቻውን የማጣራት ሂደት ለማጠናቀቅ ተሳታፊ የማህበረሰብ አበዳሪ ያገኝዎታል።
ምን ዓይነት ንግዶች ለብድር ብቁ አይደሉም?
ብቁ ያልሆኑ ንግዶች፡-
- – የካናቢስ ንግዶች ወይም ኩባንያዎች በፌዴራል ሕግ የተከለከሉ ወይም ንግዱ በሚገኝበት ሥልጣን ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸው ህጎች የተከለከሉ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች፤
- – የተገብሮ የሪል እስቴት ኢንቨስትመንቶች ወይም የዋስትናዎች ግዢ
- – በሎቢ እንቅስቃሴዎች ወይም በፒራሚድ ሽያጭ እቅዶች ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች
- – በዋናነት ለቁማር ወይም ቁማርን ለማመቻቸት የሚያገለግሉ ኩባንያዎች
- – እንደ ሸቀጦችን ወደፊት የመሸጥ ንግድ ወይም የተገብሮ ሪል ስቴት ኢንቨስትመንትን በመሳሰሉ በተለመዱ የንግድ ልውውጥ ሳይሆን በዋጋ ከፍ ዝቅ ማለት ትርፍ በሚያገኙ ግምታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች
- – የማህበረሰብ ልማት የፋይናንስ ተቋማት እና የተቀማጭ ተቋማት ወይም የባንክ ድርሻዎችን ከሚቆጣጠሩ ኩባንያዎች ካልሆኑ የጎሳ ድርጅቶች በስተቀር ከአመታዊ ገቢያቸው ከግማሽ በላይ የሚሆነውን በብድር የሚያገኙ የንግድ ድርጅቶች
- – አነስተኛ የንግድ ተበዳሪው ከሚመለከተው የግብር ባለስልጣን ጋር የክፍያ እቅድ ከሌለው በስተቀር የፌደራል ወይም የክልል የገቢ ታክስን ለመክፈል የሚፈልጉ ንግዶች
የWashington Small Business Flex Fund 2 ብድር ይቅር ሊባል የሚችል ነው?
የFlex Fund ይቅር ሊባል የሚችል የብድር ወይም የገንዘብ ድጋፍ ፕሮግራም አይደለም። በብድሩ ላይ በመመስረት ተበዳሪው የብድሩን ሙሉ መጠን ከወለድ ጋር በ3-6 ዓመታት ውስጥ መክፈል ይኖርበታል።
ክፍያ ካመለጠኝ ምን ይከሰታል?
የብድር ክፍያዎን በሰዓቱ ካላከፈሉ በማህበረሰቡ አበዳሪ ውሳኔ መሠረት የዘገየ ክፍያ ቅጣት ሊከፍሉ ይችላል። አለመክፈል ብድሩን መክፈል እንዳልተቻለ ተደርጎ እንዲገለጽ ሊያደርግ ይችላል። የብድር ማመልከቻ ሂደቱ በሚካሄድበት ወቅት የማህበረሰብ ብድር ሰጪዎ የክፍያ መዘግየት እና የብድር አለመከፈል ሁኔታ በተመለከተ ዝርዝሮችን መረዳትዎን ለማረጋገጥ የብድር ስምምነትዎ ሙሉ ውሎችን ያብራራልዎታል።